ቋሚ ኮሚቴው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የ2016 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት አገልግሎት አሰጣጥ ተመልክቷል።
በምልከታው ቋሚ ኮሚቴው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስራን ዘመኑ በሚጠይቀው ቴክኖሎጂ ከማዘመን አንጻር የተሰሩ ስራዎች፣ቅንጅታዊ አሰራር ፣የኦዲት ጉድለት ላይ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከማድረግ አንጻር የበጀት አያያዝና አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች አኳያ የተከናወኑ ስራዎች ላይ ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ ተሰጥቷል።
በመድረኩም የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ መመሪያዎችን ከማሻሻል ፣ በጀትን በፍትሃዊነት ከመደልደል፣ የአዲት ግኝት ከመስራት ባለፈ እርምጃ እንዲወሰድ ከማድረግ አኳያ ከግዥና ንብረት አያያዝ ጋር በተገናኘ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ቢሮ ኃላፊው የመንግስትን ሃብት እና በጀት በአግባቡ ማስተዳደር የእያንዳንዱ ተቋም ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ የያለውን ውስን ሃብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ቋሚ ኮሚቴው የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ቋሚ ኮሚቴው ቢሮው የፋይናንስ አሠራር ስርዓቱን ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት እና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎችን ተመልክቷል፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ ፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ኅብረተሰቡ በቅድመ በጀት ውይይቶች በመሳተፍ፣ የልማት ዕቅድ ፍላጎቶችን በመለየት ጉልህ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
መረጃዎችን ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ ፣የሴቶች ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር አበረታች ስራዎች እንደተከናወኑ ተብራርቷል።በአፈጻጸም ረገድ ስላጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያዎች ሃሳቦች ተነስተዋል።
የምክር ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትሒያ ሳኒ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስራን ለማዘመን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች፣በቢሮው ውስጥ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቁሞ የካፒታል ፕሮጀክቶች ጊዜ ገደባቸውን ጠብቀው መሄድ ይኖርበታል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።







