Harari BoFEC
No Result
View All Result
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ
No Result
View All Result
Harari BoFEC
ሃሳቦን ይስጡ
No Result
View All Result

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

July 20, 2026
in ሌሎች
0
ቋሚ ኮሚቴው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የ2016 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት አገልግሎት አሰጣጥ ተመልክቷል።
በምልከታው ቋሚ ኮሚቴው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስራን ዘመኑ በሚጠይቀው ቴክኖሎጂ ከማዘመን አንጻር የተሰሩ ስራዎች፣ቅንጅታዊ አሰራር ፣የኦዲት ጉድለት ላይ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከማድረግ አንጻር የበጀት አያያዝና አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች አኳያ የተከናወኑ ስራዎች ላይ ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ ተሰጥቷል።
በመድረኩም የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ መመሪያዎችን ከማሻሻል ፣ በጀትን በፍትሃዊነት ከመደልደል፣ የአዲት ግኝት ከመስራት ባለፈ እርምጃ እንዲወሰድ ከማድረግ አኳያ ከግዥና ንብረት አያያዝ ጋር በተገናኘ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ቢሮ ኃላፊው የመንግስትን ሃብት እና በጀት በአግባቡ ማስተዳደር የእያንዳንዱ ተቋም ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ የያለውን ውስን ሃብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ቋሚ ኮሚቴው የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ቋሚ ኮሚቴው ቢሮው የፋይናንስ አሠራር ስርዓቱን ግልፀኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት እና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎችን ተመልክቷል፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ ፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ኅብረተሰቡ በቅድመ በጀት ውይይቶች በመሳተፍ፣ የልማት ዕቅድ ፍላጎቶችን በመለየት ጉልህ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
መረጃዎችን ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ ፣የሴቶች ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር አበረታች ስራዎች እንደተከናወኑ ተብራርቷል።በአፈጻጸም ረገድ ስላጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያዎች ሃሳቦች ተነስተዋል።
የምክር ቤቱ የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፈትሒያ ሳኒ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስራን ለማዘመን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች፣በቢሮው ውስጥ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቁሞ የካፒታል ፕሮጀክቶች ጊዜ ገደባቸውን ጠብቀው መሄድ ይኖርበታል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
ShareTweetShare

ተመሳሳይ አመዶች

የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። – ጥቅምት 17/2019
ሌሎች

የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። – ጥቅምት 17/2019

October 28, 2026
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።
ሌሎች

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።

October 9, 2026
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርቱን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት አካሄደ።  * * * * * ነሐሴ 21/2018
ሌሎች

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርቱን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት አካሄደ። * * * * * ነሐሴ 21/2018

August 30, 2026
የሀረሪ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ለአቅመ-ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ሌሎች

የሀረሪ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ለአቅመ-ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

August 13, 2026
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በቢሮ ስር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ጋር የዕቅድ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ሌሎች

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በቢሮ ስር ከሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ጋር የዕቅድ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

July 20, 2026
ቢሮው የአቅመ ደካሞችን ቤት አድሶ ለባለቤቶቹ አስረከበ።
ሌሎች

ቢሮው የአቅመ ደካሞችን ቤት አድሶ ለባለቤቶቹ አስረከበ።

July 20, 2026
Load More
Next Post
ቢሮው የ2016 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡

ቢሮው የ2016 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ፡፡

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • About
  • Help
  • Feedback
  • Contact
Call us: + 251 666 0955

Copyright @ 2022 HPRS Bureau of Finance and Economic Corporation , All Rights Reserved

No Result
View All Result
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ

Copyright @ 2022 HPRS Bureau of Finance and Economic Corporation , All Rights Reserved